የሀገር ውስጥ ዜና

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ጌዲዮን (ዶ/ር) ከአፍሪካ ህብረት የፖለቲካ የሰላምና ጸጥታ ኮሚሽነር ጋር ተወያዩ

By Feven Bishaw

February 04, 2025

አዲስ አበባ፣ ጥር 27፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ጌዲዮን ጢሞቲዮስ (ዶ/ር) ከአፍሪካ ህብረት የፖለቲካ ጉዳዮች፣ የሰላምና ጸጥታ ኮሚሽነር አምባሳደር ባንኮሌ አዲኦዬ ጋር ተወያይተዋል።

 

በውይይቱ በኢትዮጵያ እና በአፍሪካ ህብረት መካከል ያለው የቆየ ትብብር ሰላምና ፀጥታን አጠናክሮ ለማስጠበቅ በሚቻልበት ሁኔታ ላይ መክረዋል።

 

ሁለቱ ወገኖች በሚቀጥለው ወር በሚካሄደው 38ኛው  የአፍሪካ ህብረት ጉባኤ ዝግጅት ዙሪያም ውይይት ማድረጋቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።