የሀገር ውስጥ ዜና

በጋምቤላ ክልል ከነገ ጀምሮ የሥራ ሰዓት ለውጥ ይደረጋል

By Feven Bishaw

February 07, 2025

 

አዲስ አበባ፣ ጥር 30፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በጋምቤላ ክልል በሙቀት መጨመር ሳቢያ የመንግስት የሥራ ሰዓት ከነገ ጀምሮ ለውጥ እንደሚደረግ የክልሉ መስተዳድር ምክር ቤት አስታወቀ።

የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ኡቶው ኡኮት እንዳሉት÷በክልሉ የሙቀቱ መጨመር ለሥራ ምቹ ባለመሆኑ ከነገ የካቲት 1 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ ለሶስት ወራት የሚቆይ የሥራ ሰዓት ለውጥ ይደረጋል።

በዚህ መሰረትም ቀደም ሲል የመደበኛው የሥራ ሰዓት ከጠዋቱ 1፡00 እስከ 6 ፡30 የነበረው ከ1፡00 እስከ 5፡30 እንደሚሆን ተናግረዋል፡፡

እንዲሁም ከሰዓት በኋላ ከ9፡00 እስከ 11፡30 የነበረው ከ10፡00 እስከ 12፡30 እንዲሆን ተወስኗል ነው ያሉት፡፡

የሥራ ሰዓት ለውጡ በማጃንግ ዞን የመንገሺና ጎደሬ ወረዳዎችን እንደማይጨምር መጠቆማቸውን የክልሉ ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመላክታል፡፡