የሀገር ውስጥ ዜና

የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ በጥር ወር በነበረበት ይቀጥላል

By Feven Bishaw

February 07, 2025

አዲስ አበባ፣ ጥር 30፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የየካቲት ወር የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ በጥር ወር በነበረበት የሚቀጥል መሆኑን የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር አስታወቀ።

 

ሚኒስቴሩ ለፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን በላከው  መግለጫ እንዳስታወቀው የየካቲት ወር 2017 ዓ.ም የሁሉም የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ጥር 2017 ዓ.ም በነበረበት የሚቀጥል ይሆናል፡፡