የሀገር ውስጥ ዜና

ጌዲዮን ጢሞቴዎስ(ዶ/ር) ከናይጄሪያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር እና ከሶማሊያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ ጋር ተወያዩ

By Feven Bishaw

February 11, 2025

አዲስ አበባ፣ የካቲት 4፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቴዎስ(ዶ/ር)  ከናይጀሪያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር የሱፍ ማይታማ ተገር ጋር  በሁለትዮሽ እና አሕጉራዊ ጉዳዮች ዙሪያ ተወያይተዋል።

 

ሚኒስትሮቹ  በውይይታቸው የሁለቱን ሀገራት ግንኙነት የበለጠ ማጠናከር በሚቻልባቸው መስኮች ላይ መክረዋል።

 

በተመሳሳይ  ጌዲዮን ጢሞቴዎስ(ዶ/ር) ከሶማሊያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አሊ ሞሀመድ ኦማር ጋር  ባደረጉት ውይይት በሁለትዮሽ እና በአካባቢያዊ የሰላም እና ጸጥታ ጉዳዮች ዙሪያ መምከራቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል፡፡