የሀገር ውስጥ ዜና

ኢትዮጵያና ሕንድ በወታደራዊ ዘርፍ በትብብር ለመስራት ተፈራረሙ

By Mikias Ayele

February 12, 2025

አዲስ አበባ፣ የካቲት 5፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ኢትዮጵያና ሕንድ በልዩ ልዩ ወታደራዊ መስኮች በትብብር መስራት የሚያስችላቸውን ስምምነት በባንጋሎር ከተማ ተፈራርመዋል።

ስምምነቱን የመከላከያ ሚኒስትር አይሻ መሃመድ (ኢ/ር) እና የሕንድ መከላከያ ሚኒስትር ራጃንታ ሲንግ ተፈራርመዋል፡፡

ስምምነቱ በአቅም ግንባታ፣ በመከላከያ ጥናትና ምርምር፣ በመከላከያ ኢንዱስትሪዎች፣ በሳይበር ደህነንነት እና ተያያዥ በሆኑ ጉዳዮች ላይ ያተኮረ ነው ተብሏል፡፡

ወታደራዊ ስምምነቱ የሁለቱን ሀገራት ታሪካዊ ግንኙነት ይበልጥ እንደሚያጠናክር ነው የተገለጸው፡፡

የመከላከያ ሚኒስትር አይሻ መሀመድ (ኢ/ር) ሕንድ ባዘጋጀችው ኤሮ ኢንዲያ 2025 በመሳተፍ ላይ መሆናቸውን የኤምባሲው መረጃ ያመላክታል፡፡