የሀገር ውስጥ ዜና

ለመስኖ ልማት አማራጭ የፋይናንስ ዘዴዎችን መለየት የሚያስችል ጉባዔ እየተካሄደ ነው

By yeshambel Mihert

February 12, 2025

አዲስ አበባ፣ የካቲት 5፣ 2017(ኤፍ ኤም ሲ) “የመስኖና ለአየር ንብረት ለውጥ የማይበገር ምርታማነት” በሚል መሪ ሃሳብ ዓለም አቀፍ ጉባዔ በአዲስ አበባ ከተማ መካሄድ ጀምሯል።

በዓይነቱ የመጀመሪያ እንደሆነ የተነገረለት ጉባኤው በዓድዋ ድል መታሰቢያ ሙዚየም ከዛሬ ጀምሮ እስከ የካቲት 7 ቀን 2017 ዓ.ም ድረስ እንደሚቆይ ተመላክቷል፡፡

በጉባዔው የተለያዩ የዓለም ሀገራት ተወካዮች እየተሳተፉ ሲሆን÷ የመስኖ ስራዎችን የሚያሳይ ኤግዚብሽን ለእይታ ክፍት ተደርጓል።

በመስኖ ልማትና አየር ንብረት ለውጥ ላይ የተሻሻለ ትብብር እና ዓለም አቀፍ ግንኙነቶች መፍጠርና ለመስኖ ልማት በመንግስት ከሚመደብ ፋይናንስ በተጨማሪ አማራጭ የፋይናንስ ዘዴዎችን ለማግኘት የሚያስችሉ ስምምነቶች በጉባዔው ይፈጠራሉ ተብሎ ይጠበቃል።

በታሪኩ ለገሰ