የሀገር ውስጥ ዜና

የኢትዮ-ጅቡቲ ኮሪደር አስተዳደር ባለስልጣን የምስረታ መድረክ ተጠናቀቀ

By yeshambel Mihert

February 12, 2025

አዲስ አበባ፣ የካቲት 5፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮ-ጅቡቲ ኮሪደር አስተዳደር ባለስልጣን የምስረታ መድረክ ዛሬ ተጠናቋል።

የኢትዮ-ጅቡቲ ኮሪደር አስተዳደር ባለስልጣን ለመመስረት የሚያስችል ጉዳዮች ላይ በጋራ የቴክኒክ ኮሚቴ ደረጃ ሰፊ ውይይት ተደርጓል፡፡

በውይይቱም የሁለትዮሽ ረቂቅ የመመስረቻ ሰነድ ላይ የተለያዩ ግብዓቶችን በመጨመር በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ ተጠናቆ ለፊርማ ዝግጁ እንዲሆን ከስምምነት ላይ ተደርሷል።

በሁለት ቀናት የውይይት ቆይታ ላይ በጋራ ለመስራት በተስሟሟቸው አጀንዳዎች ዙሪያ በመፈራረም እና የጋራ መግለጫ በመስጠት መጠናቀቁን በጅቡቲ የኢትዮጵያ ኤምባሲ መረጃ ያመለክታል።