የሀገር ውስጥ ዜና

አምባሳደር ምስጋኑ ከሶማሊያው አቻቸው ጋር ተወያዩ

By Feven Bishaw

February 13, 2025

 

አዲስ አበባ፣ የካቲት 6፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ ከሶማሊያው አቻቸው አሊ ሞሀመድ ኦማር ጋር ተወያዩ፡፡

አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ ከ46ኛው የአፍሪካ ሕብረት መደበኛ የስራ አስፈጻሚ ምክር ቤት ስብሰባ ጎን ለጎን ከሶማሊያው ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አሊ ሞሀመድ ኦማር በተለያዩ ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት አድርገዋል።

በውይይታቸው የሁለቱ አገራት ግንኙነት ከአንካራው ስምምነት መፈረም ወዲህ እየተሻሸለ መምጣቱን አንስተዋል።

ሚኒስትር ደኤታዎቹ የሁለቱን አገራት ግንኙነት በንግድ እና ኢንቨስትመንት ለማጠናከር የጋራ ኮሚሽን ስብሰባ የማድረግ አስፈላጊነት ላይ ሀሳብ መለዋወጣቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የተገኘው መረጃ አመልክቷል፡፡