የሀገር ውስጥ ዜና

የጊኒ ቢሳው ፕሬዚዳንት አዲስ አበባ ገቡ

By yeshambel Mihert

February 14, 2025

አዲስ አበባ፣ የካቲት 7፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የጊኒ ቢሳው ፕሬዚዳንት ኡማሮ ሲሶኮ ኤምባሎ በ38ኛው የአፍሪካ ሕብረት የመሪዎች ጉባዔ ላይ ለመሳተፍ አዲስ አበባ ገብተዋል።

ፕሬዚዳንቱ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ የትምህርት ሚኒስትሩ ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) አቀባበል አድርገውላቸዋል።

38ኛው የአፍሪካ ህብረት የመሪዎቸ ጉባዔ “የማካካሻ ፍትሕ ለአፍሪካውያንና ዘርዓ-አፍሪካውያን” በሚል መሪ ሀሳብ ነገ እና ከነገ በስቲያ ይካሄዳል፡፡