የሀገር ውስጥ ዜና

የኢትዮጵያ እና የአዘርባጃን ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ ተቋማት በትብብር ለመስራት ተስማሙ

By Mikias Ayele

February 14, 2025

አዲስ አበባ፣ የካቲት 7፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ እና የአዘርባጃ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ በትብብር ለመስራት የሚያስችል ስምምነት ተፈራረሙ፡፡

ስምምነቱ በተቋማቱ መካከል የዕውቀት እና ልምድ፣ ቴክኖሎጂ እና የኢንቨስትመንት ዘርፎች ላይ በትብብር ለመስራት የሚያስችል መሆኑ ተመላክቷል፡፡

በኢትዮጵያ ኢንቨስትምንት ሆልዲንግስ ዋና ስራ አስፈፃሚ ብሩክ ታዬ (ዶ/ር) እና በአዘርባጃን ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ ዋና ስራ አስፈፃሚ ራዝላን አሊካኖቭ መካከል የተፈረመው ስምምነቱ ሀገራቱ በኢከኖሚው ዘርፍ በትብብር ለመስራት ያላቸውን ቁርጠኝነት የሚያሳይ መሆኑ ተገልጿል፡፡