የሀገር ውስጥ ዜና

ኢትዮጵያ የአፍሪካ ኅብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ሆነው ለተመረጡት ማህሙድ የሱፍ የእንኳን ደስ አለዎት መልዕክት አስተላለፈች

By Feven Bishaw

February 15, 2025

 

አዲስ አበባ፣ የካቲት 8፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያ መንግስት የአፍሪካ ኅብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ሆነው ለተመረጡት የጅቡቲ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማህሙድ የሱፍ እና ለምክትላቸው ሰልማ ማሊካ ሃዳዲ የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት አስተላልፏል፡፡

የኢትዮጵያ መንግስት በመልካም ምኞት መግለጫው ለአዲስ ተመራጮቹ የኅብረቱ አመራሮች ኃላፊነታቸውን በሚገባ እንዲወጡ ያልተገደበ ድጋፍ እንደሚያደርግ አረጋግጧል፡፡

በ38ኛው የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባዔ የጅቡቲ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማህሙድ የሱፍ የአፍሪካ ኅብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ሆነው መመረጣቸው ይታወቃል፡፡