የሀገር ውስጥ ዜና

በአዲስ አበባ የፊታችን እሁድ በአንድ ቀን 2 ሚሊየን ችግኝ ሊተከል ነው

By Tibebu Kebede

July 29, 2020

አዲስ አበባ ፣ ሐምሌ 22 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዲስ አበባ ከተማ የፊታችን እሁድ በአንድ ቀን 2 ሚሊየን ችግኝ ሊተከል ነው፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ፅህፈት ቤት የፊታችን ከማለዳው 12 ሰዓት ጀምሮ በአንድ ቀን የ2 ሚሊየን ችግኝ ተከላ መርሐ ግብር እንደሚከናወን አስታወቀ።

በዚሁ የአረንጓዴ አሻራ ቀን የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪዎች እንዲሳተፉም ጥሪ አቅርቧል።