የሀገር ውስጥ ዜና

የኢትዮጵያ ሰነደ ሙዓለንዋዮች ገበያና የሩዋንዳው ስቶክ ኤክስቼንጅ በትብብር ለመስራት ተፈራረሙ

By Mikias Ayele

February 16, 2025

አዲስ አበባ፣ የካቲት 9፣2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያ ሰነደ ሙዓለንዋዮች ገበያ እና የሩዋንዳ ስቶክ ኤክስቼንጅ በትብብር መስራት የሚያስችላቸውን የመግባቢያ ስምምነት ተፈራርመዋል።

ስምምነቱ ትብብርን ለማጎልበት፣ እውቀትን ለመለዋወጥ እና አህጉራዊ የፋይናንስ ውህደትን ለማሳደግ እንደሚያስችል ነው የተገለጸው፡፡

የተቋማቱ ስልታዊ አጋርነት የገበያ ልማትን ለማጎልበት፣ በድርጅቶቹ መካከል አቅም ግንባታን ለማሳደግ እና በሁለቱም ገበያዎች አዳዲስ የኢንቨስትመንት እድሎችን ለመፍጠር ያለመ ነው ተብሏል።