የሀገር ውስጥ ዜና

ጠ/ሚ ዐቢይ (ዶ/ር) ከሶማሊያ ፕሬዚዳንት ሀሰን ሼክ መሃሙድ ጋር ተወያዩ

By Mikias Ayele

February 16, 2025

አዲስ አበባ፣ የካቲት 9፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከሶማሊያ ፕሬዚዳንት ሀሰን ሼክ መሃሙድ ጋር ተወያይተዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሑፍ÷ከሶማሊያው ፕሬዚዳንት ሀሰን ሼክ መሃሙድ  ጋር በተለያዩ ጉዳዮች ላይ መምከራቸውን አንስተዋል፡፡

የታደሰ ግንኙነት ወጥነት ያለው ሥራ ይፈልጋል ሲሊም አስገንዝበዋል፡፡

የሁለቱ መሪዎች ውይይት ሁለተኛ ቀኑን በያዘው የአፍሪካ ኅብረት 38ኛ መደበኛ ጉባኤ ጎን ለጎን ነው የተካሄደው፡፡