አዲስ አበባ፣ የካቲት 10፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያ አየር መንገድ በቻይናዋ ዢያሜን እና በብራዚሏ ሳኦፖሎ ከተሞች ካከል በሁለት ዓመትታ ብቻ ከ33 ሺህ ቶን በላይ የእቃ ጭነት ማጓጓዙን አስታወቀ።
የአየር መንገዱ ካርጎና ሎጂስቲክስ አገልግሎት ወደ ዢያሜን እና ሳኦፖሎ ከተሞች የዕቃ ጭነት አገልግሎት መስጠት የጀመረበትን ሁለተኛ ዓመት አክብሯል፡፡
በዚህ ወቅት አየር መንገዱ በሁለት ዓመታት ውስጥ በሁለቱ ከተሞች ነካከል ባደረጋቸው 474 በረራዎች 33 ሺህ 226 ቶን ያህል የዕቃ ጭነት ማጓጓዝ መቻሉ ተመላክቷል፡፡
በከተሞቹ በሚደረገው የዕቃ ጭነት አገልግሎት የኢትዮጵያ አየር መንገድ የሁለቱን አህጉራት ንግድ ትስስር ይበልጥ እያጠናከረ እንደሚገኝ ከአየር መንገዱ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡