የሀገር ውስጥ ዜና

በአማራ ብረታ ብረት ኢንዱስትሪ የተሰሩ ምርቶች ለኮሪደር ልማት ሥራ ጥቅም ላይ እየዋሉ ነው – ም/ጠ/ሚ ተመስገን

By Melaku Gedif

February 20, 2025

አዲስ አበባ፣ የካቲት 13፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በአማራ ብረታ ብረት ኢንዱስትሪና ማሽን ቴክኖሎጂ ልማት ኢንተርፕራይዝ የተሰሩ የተለያዩ ምርቶች ለኮሪደር ልማት ሥራ ጥቅም ላይ እየዋሉ ነው ሲሉ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ገለጹ፡፡

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሑፍ ÷ የአምራች ኢንዱስትሪ ዘርፉን ማስፋፋት ለምናልመው ብልጽግና ወሳኝ ነው ብለዋል፡፡

በአማራ ብረታ ብረት ኢንዱስትሪና ማሽን ቴክኖሎጂ ልማት በባሕር ዳር ከተማ የተመረቱ ስማርት ፖሎችና የዲች ከቨሮች ለኮሪደር ልማት ሥራ ጥቅም ላይ መዋል መጀመራቸውን ተናግረዋል፡፡

በተጨማሪም ኢንተርፕራይዙ የሚያመርታቸው ሌሎች ምርቶች በክልሉ እየተሰሩ ላሉ የኮሪደር ልማት ሥራዎች እያገለገሉ መሆኑን ገልጸዋል፡፡