የሀገር ውስጥ ዜና

ለ19 የአገልግሎቱ የክልል ቅርንጫፎች የተሽከርካሪ ድጋፍ ተደረገ

By ዮሐንስ ደርበው

February 21, 2025

አዲስ አበባ፣ የካቲት 14፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በጤና ሚኒስቴር፣ በኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ አገልግሎት እና አጋሮች (ግሎባል ፈንድ፣ አፍሪካ ሲዲሲ እና ጋቪ) ድጋፍ የተገዙ 62 ተሽከርካሪዎች ለኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ አገልግሎት 19 የክልል ቅርንጫፎች ተሰጡ።

ተሽከርካሪዎቹ የሕክምና ግብዓትን ተደራሽ ለማድረግ የሚያስችሉ የቀዝቃዛው ሰንሰለት ቴክኖሎጂ የተገጠመላቸው መሆናቸው ተገልጿል፡፡

እነዚህ 6 ሚሊየን ዶላር ወጪ የተደረገባቸው ዘመናዊ ተሽከርካሪዎች፤ በመድኃኒት አቅርቦትና ማጓጓዝ ላይ ከፍተኛ አዎንታዊ አበርክቶ እንዳላቸው ተመላክቷል፡፡

ርክክቡን ያከናወኑት የጤና ሚንስትር ዶክተር መቅደስ ዳባ፤ የኅብረተሰቡን የመድኃኒት ፍላጎት ለማሟላት ለምናደርገው ጥረት የተሽከርካሪዎቹ ሚና የጎላ ነው ብለዋል፡፡

በዓለምሰገድ አሳዬ