አዲስ አበባ፣ የካቲት 18፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በአማራ ክልል ደብረ ብርሀን ከተማ በ1 ቢሊዮን ብር ወጪ የተገነባው የመኪና ባትሪ ማምረቻ ፋብሪካ ተመረቀ፡፡
ሲፋን ኒው ኤነርጂ ማኑፋክቸሪንግ በተባለ ድርጅት የተገነባው ፋብሪካ የምረቃ ሥነ-ሥርዓት ላይ የኢንዱስትሪ ሚኒስትር መላኩ አለበልን ጨምሮ ከፍተኛ የመንግስት የሥራ ሀላፊዎች ተገኝተዋል፡፡
ለ110 ዜጎች የስራ ዕድል የፈጠረው ይህ የመኪና ባትሪ ማምረቻ ፋብሪካ፤ ስራ መጀመሩ ከዚህ ቀደም ከውጭ ይገባ የነበረውን ምርት በሀገር ውስጥ በመተካት ጉልህ ድርሻ ይኖረዋል ተብሏል፡፡
በአላዩ ገረመው