የሀገር ውስጥ ዜና

በቱሪዝም ዘርፍ የገበያ ፍላጎትና የሰው ኃይል አቅርቦት ላይ ምክክር ተደረገ

By ዮሐንስ ደርበው

February 26, 2025

አዲስ አበባ፣ የካቲት 19፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የሥራ እና ክኅሎት ሚኒስትር ሙፈሪሃት ካሚል እና የቱሪዝም ሚኒስትር ሰላማዊት ካሳ በሁለቱ ተቋማት መካከል በትብብር በሚከናወኑ ጉዳዮች ላይ መክረዋል፡፡

በዚህም በቱሪዝም ዘርፍ ያለው የሥራ ገበያ ፍላጎት እና የሰለጠነ የሰው ኃይል አቅርቦት ጋር ተያይዞ የተጠና ጥናት ቀርቦ በግኝቶቹና የቀጣይ ትኩረቶች ላይ መወያየታቸውን ወ/ሮ ሙፈሪሃት በማኅበራዊ ትሥሥር ገጻቸው ገልጸዋል፡፡

በቱሪዝም ኢንዱስትሪው ያለውን የአገልግሎት አሰጣጥ ማቀላጠፍ፣ ባሕላዊ ምግቦችን ወደ ሆቴሎች ሜኑ ማስገባት እንዲሁም በዘርፉ በልምድ የተገኘ ሙያን በምዘና አረጋግጦ ዕውቅና መስጠት በሚቻልበት ላይ መክረናል ብለዋል፡፡

በቀጣይም በሰው ኃይልና ቴክኖሎጂ ልማት እንዲሁም የሥራ ዕድል ፈጠራ እና ተያያዥ ጉዳዮች ላይ እንደ ተቋም በትብብር በሚከናወኑ ተግባራት ላይ መግባባታቸውን ነው ሚኒስትሯ ያመላከቱት፡፡