አዲስ አበባ፣ የካቲት 20፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢፌዲሬ ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ በናሚቢያ የቀድሞ ፕሬዚዳንት ሳም ኑጆማ ሕልፈት የተሰማቸውን ሃዘን ገለጹ።
ፕሬዚዳንት ታዬ በጽሑፍ ባስተላለፉት የሃዘን መግለጫ÷ የቀድሞ ፕሬዚዳንት ሳም ኑጆማ ናሚቢያን “መካከለኛ ገቢ ወዳለው ሀገር ያሻገሩ መሪ ተብለው ይታወሳሉ” ሲሉ አስፍረዋል።
ፕሬዚዳንት ታዬ አክለውም ሳም ኑጆማ የናሚቢያ መስራች አባት እና ሀገራቸውን የቀየሩ መሪ ነበሩ ማለታቸውን የፕሬዚዳንት ጽ/ቤት መረጃ ያመለክታል።