አዲስ አበባ፣ የካቲት 21፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በኢፌዴሪ አየር ሀይል 129ኛው የዓድዋ ድልን ምክንያት በማድረግ ባለፉት 15 ቀናት ሲካሄድ የነበረው ስፖርታዊ ውድድር የማጠናቀቂያ መርሐ-ግብር እየተካሄደ ነው።
በውድድሩ የተካሄዱት የእግር ኳስ፣ የመረብ ኳስና የገመድ ጉተታ ስፖርታዊ ክንውኖች በዛሬው እለት ፍፃሜያቸውን ያገኛሉ።
በእግር ኳስ ውድድር ማጠቃለያው የኢፌዴሪ አየር ሃይል ኤር ፖሊስ ክፍለ ጦርና በአየር ሀይል አካዳሚ ስፖርት ቡድን መካከል የዋንጫ ጨዋታ እየተደረገ ይገኛል።
በማጠቃለያ መርሐ-ግብሩ ላይ የኢፌዴሪ አየር ሀይል ዋና አዛዥ ሌተናል ጀነራል ይልማ መርዳሳን ጨምሮ የአየር ሀይል ኮማንድ ከፍተኛ አመራሮች ተገኝተዋል።
129ኛው የዓድዋ ድል በዓል “ዓድዋ የጥቁር ህዝቦች ድል” በሚል መሪ ሀሳብ ነው በተለያዩ ሁነቶች እየተከበረ ይገኛል፡፡
በዓለምሰገድ አሳዬ