የሀገር ውስጥ ዜና

ለፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን እውቅና ተሰጠ

By Melaku Gedif

February 28, 2025

አዲስ አበባ፣ የካቲት 21፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን 19ኛው የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን በዓል በስኬት እንዲጠናቀቅ በሚዲያና ኮሙኒኬሽን ዘርፍ ላበረከተው አስተዋፅኦ ከፌዴሬሽን ምክር ቤት እውቅና ተሰጥቶታል፡

እውቅናው የተበረከተው በአርባ ምንጭ ከተማ በተካሄደው በ19ኛው የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን በዓል የእውቅና እና ማጠቃለያ መድረክ ላይ ነው፡፡

ከፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን በተጨማሪም በዓሉ በስኬት እንዲጠናቀቅ አስተዋጽኦ ላበረከቱ የመገናኛ ብዙሃን፣ ክልሎች፣ የመንግስትና የግል ተቋማት እንዲሁም ግለሰቦች እውቅና ተሰጥቷል፡፡

19ኛው የብሔሮች፣ ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች ቀን በዓል “ሀገራዊ መግባባት ለሕብረ ብሔራዊ አንድነት” በሚል መሪ ሃሳብ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል አርባ ምንጭ ከተማ መከበሩ ይታወሳል፡፡