የሀገር ውስጥ ዜና

በትራፊክ አደጋ የሁለት ሰዎች ሕይዎት አለፈ

By ዮሐንስ ደርበው

February 28, 2025

አዲስ አበባ፣ የካቲት 21፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በስልጤ ዞን ወራቤ ከተማ አሥተዳደር 01 ቀበሌ ዳሎቻ ማዞሪያ አካባቢ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የሁለት ሰዎች ሕይዎት አለፈ፡፡

አደጋው የተከሰተው ዛሬ ከጠዋቱ 2 ሠዓት ገደማ መሆኑን የዞኑ ኮሙኒኬሽን መምሪያ መረጃ አመላክቷል፡፡

ከአዲስ አበባ ወደ ሆሳዕና ሲጓዝ የነበረ የደረቅ ጭነት ተሽከርካሪ በመገልበጡ የተከሰተ አደጋ መሆኑም ነው የተገለጸው፡፡