አዲስ አበባ፣ የካቲት 21፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት የብሄራዊ ደህንነት ዘርፍ አማካሪ ሚኒስትር ዴኤታ ቀንአ ያደታ (ዶ/ር) የተመራ የክትትልና ድጋፍ ቡድን አባላት በመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ተገኝቶ በዛሬው ዕለት ውይይት እና ምልከታ አድርጓል፡፡
በምልከታውም የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ለገሰ ቱሉ (ዶ/ር) ስለ ተቋሙ የስራ ክንውንና በቀጣይ ለመተግበር የታቀዱ የኮሙኒኬሽን ስራዎች ላይ ገለፃ አድርገዋል፡፡
ተቋሙ ትክክለኛና ወቅታዊ የይዘት መረጃዎችን ለሚዲያ ተቋማት የማቅረብና የመምራት፣ የሚዲያ ክትትልና ዳሰሳ የማድረግ፣ የፌዴራልና ክልል ኮሙኒኬሽን ተቋማትን የማስተባበር ተግባር እያከናወነ መሆኑን ገልጸው፤ በዚህም በዉጤት የታጀቡ ስራዎችን ማከናወን መቻሉን ተናግረዋል፡፡
የሚዲያ ዘገባዎች በሰላም ግንባታ ላይ ትኩረት እንዲያደርጉና የሁሉንም የሀገሪቱ አካባቢዎች እንቅስቃሴን በማሳየትና የሚስተዋሉ ችግሮች እንዲፈቱ ከማድረግ አኳያ በተሰራው ስራ ውጤት መገኘቱን ጠቅሰው፤ የሚዲያ ስራዎችን አጠናክሮ የማስቀጠል ስራ እንደሚሰራ ጠቁመዋል።
ተቋሙ ወቅቱን ያገናዘበ ዓላማ ተኮር የቃል አቀባይነት ሚናውን እየተወጣ እንደሚገኝ ተናግረዋል፡፡
የኮሙኒኬሽ አግባቦች ጥራት በማሳደግ ትክክለኛ፣ ፈጣንና ቀጣይነት ያለዉ የመንግስት መረጃዎች ፍሰታቸዉን ጠብቀዉ የህዝብ ተጠቃሚነትን እንዲያረጋግጡ የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት ሚና የላቀ መሆኑን ተመላክቷል፡፡
የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት ክትትልና ድጋፍ ቡድን አባላት ተዘዋውረው የአገልግቱን አሁናዊ ሁኔታ መመልከታቸውን የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት መረጃ አመልክቷል።