አዲስ አበባ፣ የካቲት 21፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በ20ኛ ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታ ኢትዮጵያ ቡና ስሑል ሽረን 1 ለ 0 በሆነ ውጤት አሸንፏል፡፡
የኢትዮጵያ ቡናን ብቸኛ የማሸነፊያ ግብ ኮንኮኒ ሀፊዝ በመጀመሪያው አጋማሽ ማስቆጠር ችሏል፡፡
ውጤቱን ተከትሎ ኢትዮጵያ ቡና በ29 ነጥብ 4ኛ ደረጃ ላይ ሲቀመጥ ሽንፈት የገጠመው ስሑል ሽረ በበኩሉ በ15 ነጥብ ባለበት 17ኛ ደረጃ ላይ ለመቆየት ተገዷል፡፡
የሊጉ ጨዋታ ምሽት 12 ሰዓት ላይ ቀጥሎ ሲደረግ ኢትዮ ኤሌክትሪክ ከአዳማ ከተማ ይገናኛሉ።