የሀገር ውስጥ ዜና

ሃብቶችን ወደ ተጨባጭ ኢኮኖሚ ለመቀየር በትኩረት ይሰራል – ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር)

By Mikias Ayele

March 01, 2025

አዲስ አበባ፣ የካቲት 22፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ተፈጥሯዊ ሃብቶችን ወደ ተጨባጭ ኢኮኖሚ ለመቀየር ልዩ ትኩረት ሰጥቶ መስራት ይገባል ሲሉ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል ርዕሰ መስተዳድር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር) ገለጹ፡፡

የክልሉን የልማት አቅምና ጸጋ መነሻ በማድረግ በተዘጋጀው የቀጣይ 3 ዓመት እቅድ ላይ ውይይት እየተካሄደ ነው፡፡

ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር) በዚህ ወቅት÷በቀጣይ ዓመታት ከመደበኛው አሠራር ለየት ባለ መልኩ ተፈጥሯዊና ሰብዓዊ ሃብቶችን ወደ ተጨባጭ ኢኮኖሚ ለመቀየር በትኩረት ይሰራል ብለዋል፡፡

ዕቅዱን እስከታችኛው መዋቅር በማውረድ እምርታዊ ለውጥ ለማምጣት የተጠናከረ የድጋፍና ክትትል ሥራ ማከናወን ይገባል ማለታቸውንም የክልሉ ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመላክታል፡፡