የሀገር ውስጥ ዜና

ኢትዮጵያ የዓለም የሚቲዎሮሎጂ ድርጅት ስልጠና ማዕከል ሆና ተመረጠች

By Mikias Ayele

March 01, 2025

አዲስ አበባ፣ የካቲት 22፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ኢትዮጵያ የዓለም የሚቲዎሮሎጂ ድርጅት የስልጠና ማዕከል ሆና መመረጧን የኢትዮጵያ ሚቲዎሮሎጂ ኢንስቲትዩት አስታውቋል።

ኢንስቲትዩቱ የአፍሪካ አህጉር የስልጠና ማዕከልን ወደ ኢትዮጵያ ለማምጣት ሲያደርግ የነበረው ጥረት በዓለም የሚቲዎሮሎጂ ድርጅት ተቀባይነት ማግኘቱ ተገልጿል።

ስኬቱ ኢትዮጵያ ዘርፈ ብዙ ሁነት እንድታስተናግድ እንደሚረዳ መገለጹን የኢትዮጵያ የሚቲዎሮሎጂ ኢንስቲትዩት መረጃ ያመላክታል።