የሀገር ውስጥ ዜና

 334 ሚሊየን ብር ግምታዊ ዋጋ ያላቸው የኮንትሮባንድ እቃዎች ተያዙ

By Mikias Ayele

March 01, 2025

አዲስ አበባ፣ የካቲት 22፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) 334 ሚሊየን ብር ግምታዊ ዋጋ ያላቸው የኮንትሮባንድ እቃዎች መያዙን የጉምሩክ ኮሚሽን አስታወቀ፡፡

ኮሚሽኑ ከየካቲት 14 እስከ 20 ቀን 2017  ዓ.ም  ባደረገው ክትትል ነው 248 ሚሊየን ብር  የገቢ እና 86 ሚሊየን ብር የወጪ ኮንትሮባንድ እቃዎች የያዘው፡፡

ከተያዙት የኮንትሮባንድ እቃዎች መካከል አልባሳት፣  ኤሌክትሮኒክስ፣ ቡና፣ ጥራጥሬ፣  የተሽከርካሪ መለዋወጫ፣ የመዋቢያ እቃዎች፣  ጫት፣ አደንዛዥ እጾች ፣ መድኃኒት፣ የቁም እንስሳት  እና የወጭ ሀገር ገንዘቦች ይገኙበታል፡፡