የሀገር ውስጥ ዜና

የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ም/ቤት አመራሮች አዲስ ኢንተርናሽናል ኮንቬንሽን ማዕከልን ጎበኙ

By Melaku Gedif

March 03, 2025

አዲስ አበባ፣ የካቲት 24፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት አመራሮችና አባላት እንዲሁም የተለያዩ ሲቪክ ማህበራት ተወካዮች አዲስ ኢንተርናሽናል ኮንቬንሽን ማዕከልን ጎብኝተዋል፡፡

በጉብኝታቸውም ማዕከሉ ኢትዮጵያን በሚመጥን ደረጃ መሰራቱ እጅግ እንዳስደሰታቸው የፖለቲካ ፓርቲ የጋራ ምክር ቤት አመራሮች ተናግረዋል፡፡፡

በቀጣይም መሰል የሀገርን ገጽታ የሚገነቡ ሥራዎች ላይ ከመንግስት ጎን በመቆም እንደሚሰሩ መግለጻቸውን የከንቲባ ጽ/ቤት መረጃ ያመላክታል፡፡