የሀገር ውስጥ ዜና

የዓለም አቀፍና ቀጣናዊ አጋር ድርጅቶች አመራሮች የሕዳሴ ግድብን ጎበኙ

By Melaku Gedif

March 03, 2025

አዲስ አበባ፣ የካቲት 24፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የዓለም አቀፍ አጋር ድርጅቶችና ቀጣናዊ አጋር ድርጅቶች አመራሮች እንዲሁም የግድብ ደህንነት ባለሞያዎች የታላቁ ኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብን ጎብኝተዋል።

በውሃና ኢነርጂ ሚኒስትር ዴዔታ አብርሃ አዱኛ (ዶ/ር) በተመራው የሕዳሴ ግድብ ጉብኝት መርሐ ግብር የተፋሰሱ ተጋሪ ሀገራት ኮሚሽነሮችና ከፍተኛ የሥራ ሃላፊዎች ተሳትፈዋል።

በተጨማሪም የካናዳና የአውስትራሊያ ግድቦች ማህበር፣ የኖርዌይ የሀይድሮፓወር ማህበር እንዲሁም የዛምቢያ ዛምቤዚ ወንዝ ባለስልጣን አመራሮች መሳተፋቸው ተገልጿል።

የጉብኝት መርሐ ግብሩ በናይል ተፋሰስ የግድብ ደህንነት ማዕከል ለማቋቋም በአዲስ አበባ የሚመክረው ዓለም አቀፍ የምክክር መድረክ አካል መሆኑን የሚኒስቴሩ መረጃ ያመለክታል።