አዲስ አበባ፣ የካቲት 24፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የተሻሻለውን የግብርናና ገጠር ልማት ፖሊሲን የማስተዋወቅ ሀገር አቀፍ መርሐ-ግብር በሲዳማ ክልል ተካሂዷል፡፡
በመርሐ-ግብሩ ላይ የግብርና ትራንስፎርሜሽን ኢንስቲትዩት ዋና ስራ አስፈፃሚ ማንደፍሮ ንጉሴ (ዶ/ር) የማሻሻያ ፖሊሲውን አስፈላጊነት በተመለከተ ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡
በዘርፉ እየተመዘገበ የሚገኘውን ስኬት ለማስቀጠል በሀገር ደረጃ እየተከናወኑ የሚገኙ ኢኒሼቲቮችና የኢኮኖሚ ማሻሻያ ሥራዎች ለፖሊሲው መሳካት መልካም አጋጣሚ መሆናቸውን የሲዳማ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር በየነ በራሳ ገልጸዋል፡፡
ፖሊሲው የገጠር ግብርናን መዋቅራዊ ሽግግር በማሳለጥ የኢትዮጵያን የብልጽግና ራዕይ ለማሳካት ቁልፍ መሳሪያ እንደሆነም ተገልጿል፡፡
ፖሊሲው እስከታች ወርዶ የታለመለትን ግብ እንዲመታ መረባረብ እንደሚያስፈልግም የጋራ አቋም መያዙን ከክልሉ ኮሙኒኬሽን የተገኘው መረጃ ያመላክታል፡፡