አዲስ አበባ፣ የካቲት 24፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የመከላከያ ሚኒስትር አይሻ መሃመድ (ኢ/ር) በመከላከያ ኢንጅነሪግ ኢንዱስትሪ ኮርፖሬሽን ስር የሚገኘውን የኤሌክትሮኒክስ ኢንጅነሪግ ኢንዱስትሪ ጎብኝተዋል።
በጉብኝታቸውም የመከላከያን ፍላጎት ለማሳካት ኢንዱስትሪው የሚያመርታቸውን የአጭር፣ መካከለኛና ረጅም ርቀት ራዲዮኖችን ተዘዋውረው ተመልክተዋል።
ሚኒስትሯ በዚህ ወቅት÷የተለያዩ ርቀት ያላቸው ራዲዮኖችን በራስ አቅም በማምረት መገጣጠም መቻላችን እንደ ሀገር ብሎም እንደተቋም ከፍተኛ አቅም እንዳለን ያሳያል ብለዋል፡፡
የተጀመረው ሥራ የሚያበረታታ መሆኑን ገልጸው÷በቀጣይ ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት አጽንኦት ሰጥተዋል፡፡
በጉብኝቱ የመከላከያ ኢንጅነሪግ ኢንዱስትሪ ኮርፖሬሽን ዋና ዳይሬክተር አቶ ጌታቸው ሃይለማሪያምና የኮርፖሬሽኑ ከፍተኛ አመራሮች መሳተፋቸውን የመከላከያ ሰራዊት መረጃ ያመላክታል፡፡