የሀገር ውስጥ ዜና

የቱሪዝም ዘርፉን ማነቃቃት የሚያስችል ስምምነት ተፈረመ

By Melaku Gedif

March 04, 2025

አዲስ አበባ፣ የካቲት 25፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያ አየር መንገድ፣ የቱሪዝም ሚኒስቴርና የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት የቱሪዝም ዘርፉን ማነቃቃት የሚያስችል ስምምነት ተፈራርመዋል።

ስምምነቱን የቱሪዝም ሚኒስትር ሰላማዊት ካሳ፣ የኢሚግሬሽን እና ዜግነት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ሰላማዊት ዳዊት እና የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ መስፍን ጣሰው ተፈራርመዋል።

ስምምነቱ ኢትዮጵያ ለስቶፕ ኦቨር ቱሪዝም ያላትን ሰፊ ዕድል መነሻ በማድረግ ዘርፉ እንዲስፋፋ፣ እንዲጎለብትና ከዘርፉ የሚገኘውን ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታ ለማሳደግ የሚያስችል የትብብር ማዕቀፍ ለመዘርጋት ያለመ ነው ተብሏል።

አቶ መስፍን ጣሠው በዚሁ ወቅት ÷የተፈረመው ስምምነት መንገደኞች ኢትዮጵያን እንዲጎበኙ ለማድረግ ጉልህ ሚና እንደሚጫወት አንስተዋል፡፡

ስምምነቱ የአዲስ አበባነ የቱሪዝም ዕድገት ለማሳደግ ታሳቢ ያደረገና በከተማዋ የቆይታ ግዜ ለሚኖራቸው መንገደኞች በተዘጋጀ ስቶፕ ኦቨር ፓኬጅ ላይ በጋራ ለመስራት እንደሚያስችል ተመላክቷል፡፡

በየሻምበል ምህረት