የሀገር ውስጥ ዜና

የሌማት ትሩፋት ለበርካታ የማህበረስብ ክፍሎች የስራ ዕድል እየፈጠረ ይገኛል – ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ

By Adimasu Aragawu

March 04, 2025

አዲስ አበባ፣ የካቲት 25፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የሌማት ትሩፋት መርሃ ግብር ለበርካታ የማህበረስብ ክፍሎች የስራ ዕድል እየፈጠረ ይገኛል ሲሉ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ገለጹ።

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት፤ የሌማት ትሩፋት መርሃ ግብር በምግብ እራስን ለመቻል ከተጀመረው ትልቅ ተግባር በተጨማሪ ለበርካታ ወጣቶች፣ ሴቶች እና ሌሎች የማህበረስብ ክፍሎች የስራ ዕድል እየፈጠረ ይገኛል ብለዋል።

በባህር ዳር ከተማም የተመለከትነው ይህንኑ ነው ሲሉ በመልዕክታቸው ገልጸዋል።