የሀገር ውስጥ ዜና

የመከላከያ ጤና ዋና መምሪያ አመራሮች አዲስ ኢንተርናሽናል ኮንቬንሽን ማዕከልን ጎበኙ

By Melaku Gedif

March 05, 2025

አዲስ አበባ፣ የካቲት 26፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የመከላከያ ጤና ዋና መምሪያ አመራሮች እና አባላት አዲስ ኢንተርናሽናል ኮንቬንሽን ማዕከልን ጎብኝተዋል።

በጉብኝት መርሐ ግብሩ የመምሪያው ሃላፊ ሌተናል ጄኔራል ጥጋቡ ይልማን ጨምሮ ሌሎች በየደረጃው ያሉ አመራሮች ተሳትፈዋል፡፡

ማዕከሉ ኢትዮጵያ የደረሰችበትን የስልጣኔ ደረጃ ያንጸባረቀና የሰራዊቱን የሀገርን ሰላም የማስጠበቅ ተልዕኮ ውጤታማነት የሚያሳይ እንደሆነ የጉብኝቱ ተሳታፊዎች መናገራቸውን የመከላከያ ሰራዊት መረጃ ያመላክታል፡፡