አዲስ አበባ፣ የካቲት 26፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የተለያዩ የሕብረተሰብ ክፍሎች አዲስ ኢንተርናሽናል ኮንቬንሽን ማዕከልን ጎብኝተዋል፡፡
በጉብኝት መርሐ ግብሩ የሃይማኖት አባቶች፣ አባ ገዳዎች፣ ሀደ ሲንቄዎች እና ነዋሪዎች መሳተፋቸውን የከንቲባ ጽ/ቤት መረጃ ያመላክታል።
የጉብኝቱ ተሳታፊዎች መንግሥት መሰል ሁለንተናዊ ፋይዳ ያላቸው መሰረተ ልማቶችን እየገነባ በመሆኑ ያላቸውን አድናቆት ገልፀዋል፡፡
ማዕከሉ የቱሪዝም ፍሰትን በማሳለጥ የኢትዮጵያን ገቢ ማሳደግ እንደሚችልም ነው የተናገሩት፡፡