የሀገር ውስጥ ዜና

ኢትዮጵያና ዴንማርክ ትብብራቸውን ለማጠናከር ተስማሙ

By Melaku Gedif

March 05, 2025

አዲስ አበባ፣ የካቲት 26፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የፕላንና ልማት ሚኒስትር ፍጹም አሰፋ (ዶ/ር) ከዴንማርክ ም/ቤት የውጭ ፖሊሲ ኮሚቴ ልዑክ ጋር ተወያይተዋል፡፡

በውይይታቸውም ኢትዮጵያ በአየር ንብረት ለውጥ ዙሪያ እያከናወነቻቸው ያሉ ኢኒሼትቮችና የተገኙ ስኬቶች ዙሪያ መክረዋል፡፡

ሁለቱ ወገኖች ሀገራቱ በተለያዩ ዘርፎች ያላቸውን ትብብር ይበልጥ ለማጠናከር መስማማታቸውንም የሚኒስቴሩ መረጃ ያመላክታል፡፡