አዲስ አበባ፣ የካቲት 26፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ሥራዎች ኮርፖሬሽን የኮንክሪት ሩፍ ታይልስ ማምረቻ ፋብሪካ የሙከራ ምርት ማምረት ጀምሯል፡፡
ፋብሪካው በሙሉ አቅሙ ወደ ሥራ ሲገባ በቀን እስከ 2 ሺህ 500 ሩፍ ታይሎችን ማምረት እንደሚችል ተገልጿል፡፡
የኮንክሪት ሩፍ ታይልስ ማምረቻ ፋብሪካ ቃሊቲ በሚገኘው የኢንዱስትሪ መንደር የተተከለ መሆኑን የኮርፖሬሽኑ መረጃ ያመላክታል፡፡