የሀገር ውስጥ ዜና

በኬንያ እስር ቤቶች የነበሩ 287 ኢትዮጵያዊያን ወደ ሀገራቸው ተመለሱ

By ዮሐንስ ደርበው

March 05, 2025

አዲስ አበባ፣ የካቲት 26፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በሕገ ወጥ የሰው አዘዋዋሪዎች ተታልለው ወደ ደቡብ አፍሪካ ለመሻገር ሲሞክሩ በኬንያ ፖሊስ ቁጥጥር ስር ውለው የነበሩ 287 ወገኖች ወደ ኢትዮጵያ ተመለሱ፡፡

እነዚህ ወገኖች በኬንያ በ18 እስር ቤቶች እንደነበሩ ተገልጿል፡፡

በኬንያ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ከኬንያ የወንጀል ምርመራ ቢሮ፣ ከኬንያ ብሔራዊ የፖሊስ አገልግሎት እና ከኬንያ ኢሚግሬሽን ቢሮ ጋር ተባብሮ ወደ ሀገራቸው እንዲመለሱ ማድረጉን በማኅበራዊ ትሥሥር ገጹ አስታውቋል፡፡

በዛሬው ዕለትም በየብስ ትራንስፖርት በሞያሌ ድንበር ወደ ሀገራቸው መመለሳቸውን ኤምባሲው አረጋግጧል፡፡