የሀገር ውስጥ ዜና

የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን የቀጣይ አንድ ዓመት አበይት ተግባራት

By Mikias Ayele

March 06, 2025

አዲስ አበባ፣ የካቲት 27፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢፌዲሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የካቲት 11 ቀን 2017 ዓ.ም በጠራው አስቸኳይ ስብሰባ የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽንን የሶስት ዓመታት የስራ አፈፃፀም በማዳመጥ እና ያልተከናወኑ ተግባራትን ከግምት ውስጥ በማስገባት የኮሚሽኑን የስራ ዘመን ለአንድ ዓመት ማራዘሙ የሚታወስ ነው፡፡

በዚህ መሰረት ኮሚሽኑ ኃላፊነቱን እንዲወጣ በተጨማሪነት በተሰጠው የአንድ ዓመት ጊዜ ውስጥ የሚከተሉትን ተግባራት ያከናውናል፡፡

ኮሚሽኑ ባለፉት ሶስት ዓመታት ባከናወናቸው ተግባራት እንደ አስፈላጊነቱ እና ድጋፍን በተጠየቀ ወቅት የተለያዩ ባለድርሻ አካላት ድጋፍ ከፍተኛ ነበር፡፡

በመጪውም አንድ ዓመት ለሚያከናውናቸውም ተግባራትም የባለድርሻ አካላት ድጋፍ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ይታመናል፡፡