የሀገር ውስጥ ዜና

የሆሚቾ ኦሙኔሽን ኢንጂነሪንግ ኢንዱስትሪ – ያለ መታከት በመሥራት የተገኘ የጋራ ውጤት!

By ዮሐንስ ደርበው

March 06, 2025

አዲስ አበባ፣ የካቲት 27፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ሆሚቾ ኦሙኔሽን ኢንጂነሪንግ ኢንዱስትሪ ያለ መታከት በመሥራት የተገኘ የጋራ ውጤት መሆኑን የተቋሙ ሥራ አሥኪያጂ ኮሎኔል ስለሽ ነገራ ገለጹ።

የሆሚቾ ኦሙኔሽን ኢንጂነሪንግ ኢንዱስትሪ አመራሮች እና ባለሙያዎች ከውጭ ተሞክሮዎችን በማምጣት እና ሥልጠና በመሥጠት ያለ መታከት ቀን ከሌሊት በመሥራት ያስገኙት የጋራ ውጤት ነው ብለዋል ሥራ አስኪጁ፡፡

ፋብሪካው ዘመኑ በደረሰበት የዲጂታል ሥርዓት ውስጥ ገብቶ፣ ለከባድ፣ ቀላልና መካከለኛ መሣሪያ ተተኳሾችን ማምረት ጀምሯል ማለታቸውን የመከላከያ ሠራዊት ማኅበራዊ ትሥሥር ገጽ መረጃ አመላክቷል፡፡

ከሀገሪቱ የአቅርቦት ፍላጎት በላይ የውጭ ገበያንና ትውልድን ታሳቢ በማድረግ መገንባቱንም አስረድተዋል።

የሆሚቾ ኦሙኔሽን ኢንጂነሪንግ ኢንዱስትሪ የተለያዩ ተተኳሾችን በማምረት፤ የተቋቋመበትን ዓላማ በማሣካት ላይ የሚገኝ ኢንዱስትሪ መሆኑንም ገልጸዋል፡፡

ኢንዱስትሪው አሁን ካለበት ዐቅም ከስምንት እጥፍ በላይ ተተኳሾችን ማምረት እንዲችል ተደርጎ መገንባቱንም ተናግረዋል፡፡