የሀገር ውስጥ ዜና

በኮምቦልቻ በግማሽ ቢሊየን ብር ወጪ የንጹህ መጠጥ ውኃ ፕሮጀክት እየተገነባ ነው

By Hailemaryam Tegegn

March 07, 2025

አዲስ አበባ፣ የካቲት 28፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በአማራ ክልል ኮምቦልቻ ከተማ አሥተዳደር በ515 ሚሊየን ብር ወጪ የንጹህ መጠጥ ውኃ ፕሮጀክት ግንባታ እየተከናወነ መሆኑ ተገለጸ፡፡

የክልሉ ውኃና ኢነርጂ ቢሮ ኃላፊ ማማሩ አያሌው (ዶ/ር) የፕሮጀክቱን የግንባታ ሂደት የጎበኙ ሲሆን፤ በዚሁ ወቅት ፕሮጀክቱ የከተማዋን የኢንቨስትመንትና የወደፊት ዕድገትና ታሳቢ ያደረገ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

ግንባታው እየተከናወነ የሚገኘው በዋተር ፈንድና በከተማ አሥተዳደሩ ትብብር መሆኑን የአማራ ክልል ኮሙኒኬሽን ቢሮ መረጃ አመላክቷል፡፡

ፕሮጀክቱ አምስት ጥልቅ ጉድጓዶች የሚኖሩት ሲሆን፤ ሦስቱ ሙሉ በሙሉ መጠናቀቃቸው ተገልጿል።

ይህም አሁን ያለውን የከተማዋን የውኃ ሽፋን ከነበረበት ወደ መቶ በመቶ እንደሚያሳድገው ነው የተገለጸው፡፡