አዲስ አበባ፣ የካቲት 28፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የብልጽግና ፓርቲ የክልልና ከተማ አስተዳደር ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ከፍተኛ አመራሮች የፓርቲውን ዋና ጽ/ቤት የተቋም ግንባታ እንቅስቃሴ ጎብኝተዋል፡፡
በጉብኝታቸውም በፓርቲው ዋና ጽ/ቤት የተሰሩ የፓርቲ ዶክመንቴሽን፣ የሚዲያ ስቱዲዮ፣ ቤተ መጻሕፍትና ጅምናዚዬም ግንባታዎችን ተዘዋውረው ተመልክተዋል።
አመራሮቹ በዋናው ጽ/ቤት ያለውን መልካም ተሞክሮ በየክልሎቻቸው በመተግበር ሁለንተናዊ የፓርቲ ተቋም ግንባታን እውን ለማድረግ እንደሚሰሩ ማረጋገጣቸውን የፓርቲው መረጃ ያመላክታል፡፡