የሀገር ውስጥ ዜና

‘ቸርነት ሀሪፎ ማን ነው?

By ዮሐንስ ደርበው

March 08, 2025

አዲስ አበባ፣ የካቲት 29፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ወጣቱ ኢትዮጵያዊ ዲፕሎማት ቸርነት ሀሪፎ በተባበሩት መንግሥታት የምሥራቅ አፍሪካ የልማት በይነ-መንግሥታት (ኢጋድ) ቋሚ ተወካይ ሆኖ ተሹሟል፡፡

ለመሆኑ ይህ ወጣት ማን ነው….?

👉 በልጅነቱ ወደ ኬንያ ያቀናው ቸርነት ሀሪፎ፤ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርቱን በናይሮቢ ኪሊማኒ ትምህርት ቤት ተከታትሏል፡፡

👉 ከዚያም ወደ አሜሪካ አምርቶ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርቱን በፔንስልቬንያ ሎወር ሜሪዮን ትምህርት ቤት ተምሯል፡፡

👉 በትምህርት ቤቱ ባገኘው የትምህርት ዕድል (ስኮላርሺፕ) አማካኝነትም ቴምፕል ዩኒቨርሲቲን መቀላቀል ችሏል።

👉 ወጣቱ ዲፕሎማት በፖለቲካል ሣይንስና ሕግ ትምህርት የመጀመሪያ ዲግሪውን ከአሜሪካው ቴምፕል ዩኒቨርሲቲ አግኝቷል።

👉 በአሁኑ ወቅትም በፔንስልቬንያ ዩኒቨርሲቲ የማስተርስ ዲግሪ ትምህርቱን በፐብሊክ አድሚኒስትሬሽን እየተከታተለ እንደሚገኝ በተባበሩት መንግሥታት ድረ-ገጽ ላይ የሰፈረው መረጃ ያመለክታል።

👉 ከአሁን ቀደም በተለይም በስደተኞችና በትምህርት ጉዳይ የተባበሩት መንግሥታትን ጨምሮ በዓለም አቀፍ መድረኮች በንቃት ሲሳተፍ መቆየቱም ተጠቅሷል፡፡

👉 ይህ ዲፕሎማት ሥድስት ቋንቋዎችን ማለትም አማርኛ፣ ኦሮምኛ፣ ትግርኛ፣ ስዋሂሊ፣ እንግሊዝኛ እና ፈረንሳይኛ አቀላጥፎ እንደሚናገር ገልጿል።

👉  ወጣቱ ኢትዮጵያዊ ዲፕሎማት ቸርነት ሀሪፎ በተባበሩት መንግሥታት የምሥራቅ አፍሪካ የልማት በይነ-መንግሥታት (ኢጋድ) ቋሚ ተወካይ ሆኖ ተሹሟል፡፡

👉  የሹመት ደብዳቤውንም ለመንግሥታቱ ዋና ፀሐፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ አቅርቧል።

በኃይለማርያም ተገኝ