አዲስ አበባ፣ የካቲት 29፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) 22ኛው የኢትዮጵያ የባህል ስፖርቶች ውድድር እና 18ኛው የባህል ፌስቲቫል በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሆሳዕና ከተማ መካሄድ ጀምሯል፡፡
ከየካቲት 29 እስከ መጋቢት 7 ቀን 2017 ድረስ የሚካሄደው ይህ መርሐ-ግብር፤ “ባህላዊ ስፖርቶቻችን ለጠንካራ ኅብረ-ብሄራዊ አንድነታችን” በሚል መሪ ሐሳብ ዛሬ ተጀምሯል፡፡
በውድድሩ ከ11 ክልሎችና ሁለት ከተማ አሥተዳደሮች የተወጣጡ 1 ሺህ 386 ስፖርተኞች በ11 ባህላዊ ስፖርቶች ይሳተፋሉ።
በውድድሩ ሕግ እና ደንብ የተዘጋጀለት የአፋር ኮኢሶ የተባለ አዲስ ስፖርታዊ ውድድር ዘንድሮ ይተዋወቃል የተባለ ሲሆን፤ በቀጣይ ዓመት ውድድር ላይ እንደሚካተት ተነግሯል።
በትዝታ ወንድሙ