የሀገር ውስጥ ዜና

72ኛው የቦረና ገዳ ባሊ ስልጣን ርክክብ ሥነ ሥርዓት ዛሬ ይካሄዳል

By Melaku Gedif

March 09, 2025

አዲስ አበባ፣ የካቲት 30፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) 72ኛው የቦረና ገዳ ባሊ ስልጣን ርክክብ ሥነ ሥርዓት በዛሬው ዕለት ይካሄዳል፡፡

በርክክብ ሥነ ሥርዓቱ የፌዴራል እና የክልል ከፍተኛ የሥራ ሃላፊዎችን ጨምሮ የኬንያ ልዑካን ቡድን አባላት እንደሚታደሙ ይጠበቃል፡፡

72ኛው የቦረና ገዳ ባሊ ስልጣን ርክክብ ሥነ-ሥርዓት ከየካቲት 25 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ በተለያዩ ሁነቶች እየተካሄደ ይገኛል፡፡