የሀገር ውስጥ ዜና

የመደመር ዕሳቤን መሠረት በማድረግ አንድነትን ማጠናከር እንደሚገባ ተመላከተ

By Mikias Ayele

March 10, 2025

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 1፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ‎የመደመር ዕሳቤ እና የብልጽግና መርሆዎችን መሠረት በማድረግ ውስጣዊ አንድነታችንን ማጠናከር አለብን ሲሉ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመንግሥት ዋና ተጠሪ ሚኒስትር ተስፋዬ በልጅጌ (ዶ/ር) ተናገሩ።

‎‎የጎፋ እና ኦይዳ ሕዝብ የአንድነትና ወንድማማችነት ማጠናከሪያ ምክክር መድረክ የሣውላ ቃል ኪዳን በሚል ስያሜ ባለ ዘጠኝ ነጥብ የአቋም መግለጫ በማውጣት ተጠናቅቋል፡፡

‎መድረኩ በዋናነት የመደመር ዕሳቤ እና የብልጽግና መርሆዎችን ታሳቢ ያደረገ መሆኑን ሚኒስትሩ ገልጸዋል፡፡

በተጨማሪም መከባበርና መተሳሰብ፣ የዞኑን ሕዝብ አንድነትና አብሮነት ማዕከል ያደረገ እና የተሰጠውን ዕድል በአግባቡ የሚጠቀም ትውልድ ለመፍጠር የተዘጋጀ መሆኑን አንስተዋል፡፡

‎አንድነትን በማጠናከር ሕዝቡን መካስ እንደሚገባ ማስገንዘባቸውን የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ኮሙኒኬሽን ቢሮ መረጃ አመላክቷል፡፡