የሀገር ውስጥ ዜና

ቻይና በኢትዮጵያ የኢንቨስትመንት ተሳትፎዋን ለማሳደግ ቁርጠኛ መሆኗን ገለጸች

By Hailemaryam Tegegn

March 11, 2025

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 2፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ገዥ ማሞ ምህረቱ በኢትዮጵያ ከቻይና አምባሳደር ቼን ሀይ ጋር ተወያይተዋል፡፡

በውይይታቸውም በብሪክስ የትብብር ማዕቀፍ መሠረት የሁለቱን ሀገራት ትብብር ለማጠናከርና በማደግ ላይ ያሉ ሀገራትን ጥቅም ለማስጠበቅ በጋራ መስራት አስፈላጊ መሆኑን አንስተዋል፡፡

አምባሳደር ቼን ሀይ÷ ሀገራቸው የኢትዮጵያን የኢኮኖሚ ሪፎርም እንደምትደግፍና የኢንቨስትመንት ተሳትፎዋንም ለማሳደግ ቁርጠኛ እንደሆነች ማረጋገጣቸውን ከቻይና ኢምባሲ ያገኘነው መረጃ አመላክቷል፡፡