የሀገር ውስጥ ዜና

ሕብረተሰቡ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ጥያቄዎቹን እንዲያቀርብ ጥሪ ቀረበ

By ዮሐንስ ደርበው

March 11, 2025

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 2፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ሕብረተሰቡ በትምህርት፣ በጤና፣ በኢኮኖሚ ጉዳዮችና አምራች ዘርፎች ላይ ጥያቄዎቹንና ማብራሪያ የሚሹ ጉዳዮችን እንዲያቀርብ የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ጥሪ አቀረበ፡፡

በዚሁ መሠረት ሕብረተሰቡ በጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት የማኅበራዊ ትሥሥር ገጾች አማካኝነት ጥያቄዎቹን መላክ እንደሚችል ተገልጿል፡፡

ለሚቀርቡ ጥያቄዎችም የሚመለከታቸው የሥራ ኃላፊዎች ምላሽና ማብራሪያ እንደሚሰጡበት ጽሕፈት ቤቱ በማኅበራዊ ትሥሥር ገጹ አረጋግጧል፡፡