አዲስ አበባ፣ መጋቢት 3፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በትብብር የቱሪዝም ሀብቶችን በማልማትና በማስተዋወቅ ዘላቂ ተጠቃሚነትን ማረጋገጥ ይገባል ሲሉ የቱሪዝም ሚኒስትር ሰላማዊት ካሳ ገለጹ፡፡
የቱሪዝም ዘርፉ የ2017 በጀት ዓመት የመጀመሪያ መንፈቅ ዓመት ዕቅድ አፈፃፀም መድረክ እየተካሄደ ነው፡፡
ሚኒስትሯ በመድረኩ ላይ ባደረጉት ንግግር፤ የቱሪዝም ልማት ጥምረትና ቅንጅት የሚፈልግ በመሆኑ በትብብር የቱሪዝም ሀብቶችን በማልማትና በማስተዋወቅ ዘላቂ ተጠቃሚነትን ማረጋገጥ ይገባል፡፡
ባለፉት ሥድስት ወራት በአምስት መዳረሻዎች ላይ ዕሴት የመጨመር ሥራ መሠራቱን ጠቅሰዋል፡፡
በሌላ በኩል ኢትዮጵያን ከጎበኙ 661 ሺህ 870 የውጭ ሀገር ጎብኚዎች 2 ነጥብ 4 ቢሊየን ዶላር ገቢ መገኘቱን ተናግረዋል፡፡
በቱሪዝም ዘርፉ ለ40 ሺህ 89 ዜጎች የሥራ ዕድል መፍጠር መቻሉንም አንስተዋል፡፡
በፍቅርተ ከበደ